- Aute irure dolor in reprehenderit.
- Occaecat cupidatat non proident sunt in culpa.
- Pariatur enim ipsam.
ከሶማሌላንድ የባህር በር ለማግኘት እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴ መጠኑ ያልተገለጸ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የአክሲዮን ድርሻ ሊሰጥ ይችላል በሚለው ጉዳይ ላይ፣ የተላለፈ መመርያም ሆነ መንግሥታዊ አቅጣጫ እንደሌለና በሐሳብ ደረጃ ብቻ የተያዘ መሆኑ ታወቀ።
መንግሥት የአገሪቱን ጥቅሞች በማስጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና አለው በሚል የተለያዩ ዕርምጃዎችን እየወሰደ ባለበት የወደብ ባለቤትነት ጉዳይ፣ የመጀመሪያው ዕርምጃ ነው የተባለለትን የመግባቢያ ስምምነት ታኅሳስ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ መፈራረማቸው ይታወሳል።
ሁለቱ የስምምነቱ አካላት ውሉን መፈጸማቸውን ይፋ ያደረጉት የመግባቢያ ሰነድ ቃል በቃል ምን እንደሚል ለሕዝብ በይፋ ግልጽ ባይደረግም፣ ከፊርማው በኋላ በወጡ መግለጫዎችና ሪፖርቶች ግን ሁለት ጉዳዮች ጎልተው ሲወጡ ተስተውለዋል።
ከእነዚህ ሁለት መላምቶች በአንዱ ኢትዮጵያ ለምትቀበለው የባህር በር ምላሽ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአገርነት ዕውቅና ላልተሰጣት ሶማሌላንድ የአገርነት ዕውቅና ልትሰጥ ትችላለች የሚለው ተቀዳሚው ሲሆን፣ ተከታዩ ደግሞ ሶማሌላንድ በአፍሪካ ተቀዳሚ ትርፋማ ከሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የአክሲዮን ድርሻ ልትወስድ ትችላለች የሚል እንደሆነ መዘገባችን ይታወሳል።
ebookSpot
የዓድዋ ድል በዓል ባለቤትነት ለመከላከያ ሚኒስቴር መሰጠቱ በፓርላማ ጥያቄ አስነሳ
የዓድዋ ድል በዓል አከባበር ኃላፊነትና ባለቤትነት የተሰጠው የመከላከያ ሚኒስቴር በፓርላማ ጥያቄ ተነሳበት፡፡
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ የማኅበራዊ ልማት፣ የባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የሕዝብ በዓላትንና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ን በሚመለከት ከአስረጂዎች ጋር ሰኞ መጋቢት 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ውይይት ሲደረግ የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን፣ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ኃላፊዎች የዓድዋ ድል በዓል ባለቤትነት ለመከላከያ ሚኒስቴር በመሰጠቱ ጥያቄ አንስተዋል፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች የዓድዋ በዓል ነፃነት፣ እኩልነትና አብሮነት የታየበት በመሆኑ፣ ማኅበራዊ አንድነትን በማጠናከር የጋራ እሴቶችን ለትውልድ ለማስተላለፍ ታሪካዊ ይዘቱን ጠብቆ፣ በተለያዩ የጥበብ ሥራዎች የሚከበር በመሆኑ፣ በዓሉን የማስተባበር ሥራ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ የሚመሩት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አጀንዳ አድርጎ የያዘው ወቅታዊ የፀጥታና የደኅንነት ጉዳዮች ውይይት ከመጀመሩ በፊት ተጨማሪ አጀንዳ ማስያዝ የምትፈልጉ ሲባል በሙስና የሚጠረጠሩት ኃላፊ እጃቸውን አወጡ
አስጎብኚ ድርጅቶች ለጥያቄያቸው ምላሽ ሳያገኙ እንደገና ተመዝገቡ መባላቸውን ተቃወሙ
Excepteur sint occaecat cupidatat non proident sunt in culpa qui officia deserunt mollit anim id est laborum. Sed ut perspiciatis unde omnis iste natus error sit voluptatem accusantium doloremque laudantium totam rem aperiam.
ሲያቀርቧቸው የነበሩ ጥያቄዎች ምላሽ ሳያገኙ እንደገና ‹‹ተመዝገቡ›› መባሉ፣ ተገቢ እንዳልሆነ አስጎብኚ ድርጅቶች አስታወቁ፡፡
ቀደም ሲል አስጎብኚ ድርጅቶች ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሳይሰጥባቸው የቱሪዝም ሚኒስቴር ዳግም ምዝገባ እንዲካሄድ መጠየቁ አግባብ አለመሆኑን፣ የታላቁ የኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅቶች ማኅበር ገልጿል፡፡

